ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን ሃዋርያው ጳውሎስ በጻፈው መለእክት እደተገለጠ ሁሉን በክርስቶስ ኢየሱስ ተጠቅልሎ ማየት ነው።
"በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።" ኤፌ 1፡ 9-10
መጽሐፍ ቅዱስ፡- ብሉይ እና አዲስ ኪዳንን ያቀፈ በመንፈስ ቅዱስ አብርሆት የተጻፈ ስልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን። እግዚአብሔርን ለሰው ልጆች የማዳን እቅድን የሚገልጽ እና የእምነት እና የእግዚአብሄር ህዝብ ተግባር የመጨረሻ መመሪያችን እንደሆነ እናምናለን።
እግዚአብሔር፡- በሦስት አካላት ማለትም በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ለዘላለም በሚኖር ፤ ሁሉን በሚችል ፤ ሁሉን በሚያውቅ ፤በአንድ ግዜ በሁሉ ስፍራ በሚገኝ፤ በማይለውጥ ፤ ምጡቅም ቅርብም በሆነ ቅዱስ እና እውነተኛ ጻድቅም ፍቅርም በሆነ አንድ አምላክ እናምናለን—እያንዳንዳቸው ሙሉ በሙሉ እና አንድ አይነት በሆነ አምላካዊ ባህሪ የሚኖሩ፣ ነገር ግን በአካል እና በተግባር የተለዩ ናቸው።
እግዚአብሔር አብ፦ የሥላሴ የመጀመሪያ አካል ሆኖ ይታያል—አንድ እውነተኛ አምላክ ለዘላለም የሚኖር፣ ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን የሚያውቅ እና በሁሉም ቦታ የሚገኝ ነው፡፡ እንደ አባት እርሱ የአጽናፈ ሰማይ ፈጣሪ እና ደጋፊ ነው፡፡ የህይወት እና የፍቅር ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ የአብ ፍቅር ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን የሰው ልጆችን እንዲቤዥ እና አማኞችን ለማበረታታት እና ለመምራት መንፈሱን በመላክ ተገልጧል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ፡- በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን ከአምላክ በተገኘ አምላክ የእግዚአብሄር ልጅ በሆነ ከድንግል በተወለደ በፍጹም ሰውነት እና አምላክነት ሳይነጣጠል እና ሳይደባለቅ በአንድ አካል በተገለጠ፣ ኃጢአት በሌለበት ውልደቱ እና ሕይወቱ፣ በመስቀል ላይ በምትክነት የመሰዋት ሞትን በሞተ በተቀበረ በሶስተኛውም ቀን በከበረ ስጋ በተነሳ ፣ ወደ ሰማይ ባረገ፣ ዳግም ተመልሶ በኃይልና በክብር በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ በሚመጣ እናምናለን።
መንፈስ ቅዱስ፡- በመንፈስ ቅዱስ በፍጹም አምላካዊ ባህሪ በአካልና ሥራ እናምናለን፣ ዓለምን በኃጢያት የሚወቅስ፣ የሚድኑትን የሚረዳ አማኞችን የሚያድስ እና በአማኞች በሚያድር፣ ለክርስቲያናዊ ኑሮ እና አገልግሎት ምሪትን እና ኃይልን በሚሰጥ ለቤተ ክርስቲያን መታነጽ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሚሰጥ እናምናለን።
መዳን፡- መዳን በጸጋ ብቻ፣ በእምነት ብቻ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ እናምናለን። ከእግዚአብሔር ጋር የመታረቅ እና የዘላለም ሕይወት ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ፤ ንስሃ በመግባት ከመንፈስ እና ከቃሉ ውሃ (ከመስቀሉ ውሃ) ዳግም በመወለድ የሚገኝ የእግዚአብሄር ልጅነት እድሆነ እናምናለን።
ቤተ ክርስቲያን፡- በአንዲት ሁለንተናዊ ቤተ ክርስቲያን፣ የክርስቶስ አካል እና ሙሽራ በሆነች ሁሉንም እውነተኛ አማኞች ባቀፈች እና የክርስቶስ አካል በምድር ላይ በሚታይባት: በገዛ ደሙ በተዋጁ የቅዱሳን ህብረት እና አንድነት ባለባት፣ መንፈስ ቅዱስ በሚሰራባት በአጥቢያ ቤተ ክስቲያን እናምናለን።
የአማኞች ንጥቀት የሙታን ትንሳኤ እና ዳግም ምጻት፡- በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ በክብር መምጣት፣ በአማኞች ንጥቀት በሙታንም ትንሳኤ፣ በመጨረሻው ፍርድ እና በእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግስት መመስረት እናምናለን። በጉጉት የምንጠብቀው የተባረከውን የክርስቶስን መምጣት ተስፋ እና በእርሱም የሁሉም ፍጻሜ እና የአዲስ ፍጥረት እና ስርአት ጅማሬ እደሚሆን እናምናለን።
መላእክት፤ በቅዱሳን መላእክት የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሚያገልግሉ መኖር እናምናለን፡፡ በትዕቢት ምክንያት በተጣሉ መላእክት የቅዱሳኑም ጠላት በሆኑ፡ ክርስቶስም አለቅነታቸውን እና ስልጣናቸውን በገፈፋቸው መኖር እናምናለን።
በቤተ ክርስቲያን የሚደረጉ ቅዱስ ሥርዓት ፡-
በታልቁ ተልእኮ ፡ በዚህ አለም ወደሚኖሩ ህዝቦች በተላከ ሰዎችን በሚያድን የእግዚአብሔር ወንጌል፡ ደቀ መዝሙር በማድረግ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ሃይል በወንጌል ስርጭት ተልእኮ እና ርህራሄ በሚያሳይ በታላቁ ተልዕኮ ስልጣን እናምናለን።
የእግዚአብሄር መንግስት ስነ ምግባር
የቤተ ክርስቲያን ባህል
የቤተ ክርስቲያን ባህል የሚመሰረተው በክርስቶስ አማኝ ሁሉ የተደረገውን በመረዳት እና በማመን ሲሆን የሚገነባው ደግሞ ስለ ክርስቶስ የሚያደርገውን በመረዳት እና ተግባራዊ በማድረግ ነው።
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.